ጀግን የኔ ልጅ ግድ የለህም ጀግን

እኔ ጀግን ስልህ የዓለም የማህበረሰብ ጥናት ግን ራስህን ሁን ይልሃል። በሁለቱ መካከል ስላለው ልዩነት ልንገርህ? ዓለም ማንነትህን ተፈጥሮአዊ አረዳድህን በእርሷ ዝቃጭ አንድም አጣፍጣ አንድም በቲፎዞ(በድምጽ ብልጫ) ስትበርዝህ እና ስትሞላህ ትቆይና ቃሉ በራሱ ስህተት የሌለበትን “ራስህን ሁን” የሚል መፈክር ዘወትር ታስደግምሃለች።ራስህን መሆን ቃሉ በራሱ ትክክል እና ተገቢ ሆኖ ሳለ አንተ ግን አሁን ያለህበት ማንንነት እውን ራስህን ሁን ያስብልሃል ወይ? የኔ ጥያቄ ነው።
ዛሬ ላይ የአንተ አእመሮ ከመሥሪያ ቤት እስከ መኖሪያ ቤት፣ከገበያ ቦታዎች እስከ መዝናኛ፣ ከመጓጓዣ እስከ ሕክምና አገልግሎቶች፣ ከማሕበራዊ እስከ ፖለቲካዊ ጉዳዮች …….በቤትህም ከእልፍኝህ እስከ መኝታህ የሚታየው በእኩልነት ቅኝት የተቀነቀነ ዘፈን፣ቁምነገር እና ጨዋታ ሞልቶትነው። ከዚህም የተነሳ የሰንበት ውሎህን እንኳ ራስህን ችለህ ማቀድ ተስኖህ የሚስትህን ይሁንታ የምትጠብቅ ከሆነ ራስህን ሁን ማለት ላንተ ስህተት ይሆናል።
አስረጅ፦በሰሜን አሜሪካ በባርያ ፍንገላው የመጨረሻው ዘመን የእነ አብርሃም ሊንከን ጦር የኮንፌደሬቱን አሸንፎ ለደቡባውያኑ ባሪያዎች የነጻነት ዜና አበሠረ። ነገር ግን የተወሰኑ በባርነት ቀንበር ስር የነበሩ ሰዎች እውነትነቱን ተጠራጠሩ(ይሄ እንዴት ይሆናል ብለው) ጌቶቻቸው እንዲሄዱ ግድ ቢሏቸውም(ያስቀጣቸዋልና) እነርሱ ግን ባርነታቸውን ፈቀዱ። ለእነዚህ “ባሪያዎች” እንግዲህ ነጻ ወጥታችኋል ብሎ መለፈፍ ብቻውን ዋጋ አልነበረውም ይልቅስ ነፃነት ሰዎች ያለችሮታ ሰው ስለሆኑ ብቻ ሊያገኙት የተገባ መሆኑን ማስረዳት እንጂ። አንድ ወዳጄ ይህንን ሳጫውተው ምን አሜሪካ አስኬደህ እዚህ እኛ ሰፈር ከአፄው ሥርዓት ጀምሮ ጫማ እንኳን ሳያደርጉ በባርነት ጌታቸውን የሚያገለግሉ አዛውንት አሉ ብሎኝ እርፍ። እነዚህ ሰዎች የባርያ ፈንግሉ አመለካከት ደማቸውን ከመዋሃዱ የተነሳ ምንም እንኳ የነፃነቱን ዓዋጅ ቢሰሙትም በነበሩበት ማሕበረሰብ ውስጥ ግን ተፈጻሚ የሚሆን አይመስላቸውም ቢፈጸምም እንኳ አሁን ካሉበት ነባራዊ ሁኔታ ተሽሎ አይታያቸውም።ለነእርሱ ባርነት እንዲህ ተዋህዷቸው ነጮችን፣ ጌቶችን ወይም ሰውን አይታችሁ አለልካችሁ ከመንጠራራት፣ከመዝለል ራሳችሁን ሁኑ ብትሏቸው ምን ይሆናሉ? አዎ ራሳቸውን ሲያዩ ባሪያ፥ መሆን የፈለጉት ጌታ ስለዚህ ራስንመሆን መልካም ከሆነ ባርነትን ተቀብሎ ከመኖር ውጪ አማራጭ የለምና የተመሰገነ የተወደደ(በዋጋ) ባሪያ ለመሆን ይተጋሉ።:
ይህንን ማስረጃ ወደ እኛ ኃሳብ ይዘነው እንምጣና ዛሬ ላይ ታዲያ ምን ያክል ሰው ነው ራስህን ሁን ስትሉት ተፈጥሮአዊ ማንነቱን (ከፈጣሪ የተቸረውን)ለመረዳትና ለማወቅ የሚጥረው? ብዙዎቻችን እኮ የምዕራብያውያን የልዩነት መርዝ፣ የፉክክር ትምህርት (በሀገራችን፣ በባሕላችን፣ በኃይማኖታችን፣ በትዳራችን፣ በጾታችን፣በቤታችን፣ በሥልጣኔያችን…..ወዘተርፈ) የባይተዋርነት መንፈስ በውስጣችን በደማችን አስፍኗል። እውነት ተሸፍና ሳለ ደጋግመን በመገናኛ ብዙኃኑ የሰማናቸውን ውሸቶች እውነት ናቸው ብለን ተቀብለናል። በዚህም ምክንያት ወንዶች እንኳ ተፈጥሮአዊው ማንነታችን እንዲህ ነው ሲባሉ አልዋጥ ይላቸዋል።
ዓለም እንዴት ተፈጥሮህን በርዛ(መርዛ)፣ ከፈጣሪህ ለይታ፣ ራስህን አሳጥታህ፣ እንደምታጎሳቁልህ ልንገርህ? አንተ አባወራነት ተፈጥሮአዊ ፣ስጦታህም ሆነ ግዴታህ ነው፣ ተለማመደው ስልህ እንዴት ይሆናል ትላለህ። እርሱንም መለማመድ አትፈልግምና ሚስትህን መምራት ትተህ ካልመራሺኝ ወይም አብረን እንምራ ትላለህ። ይህ ጠባይህ ለሴቷ ሴትነት አቻ አይሆንምና እርሷ ላንተ ያላት የወሲብ ዝንባሌ ይቀዘቅዛል።ምክንያቱም የተሳካ ተራክቦ አወቅን ባዮቹ የእኩልነት አራጋቢዎች እንደሚሉት በንግግር፣ በድርድር እና በምክክር የሚፈጸም ሳይሆን የሚስትን ስሜት በመረዳት፣ በመምራት (በመግራት)፣ እና ከእርካታው ጥግ በማድረስ ነው። ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን ቀናት በሳምንታት ሳምንታት በወራት ወራት በዓመታት ሲተኩ ሚስትህ በትንሽ ትልቁ ንጭንጭ ታመጣለች። አንተ አብረሃት ትተኛለህ ነገርግን ጨዋታህ እርሷን የማያሳትፍ ወይምየማያሳርፍ ይሆንና ሩጫህ ሁሉ ላንተ ደስታ ይሆናል። በዚህም ምክንያት ነው ብዙዎቹ ሴቶች ወንዶችን ምን ገንዘብ(ስጦታ) ቢሰጧቸው ምን ልጆቻቸውን ቢንከባከቡ….. ራስወዳድ ናቸው ብለው የሚፈርጇቸው። እነዚህ ወንዶች ታዲያ ባልገባቸው እና ባልተረዱት የሚስቶቻቸው ፍላጎት ናላቸው ይዞራል። “ሁሉን ፣ያለኝን ሰጠኋት እንግዲህ ምን ልሁን ?ምን አድርግ እንደምትለኝ ግራገባኝ” ሲሉ ይደመጣሉ ተረክቦአዊ ግንኙነታቸውም ያሽቆለቁላል። ይህም ሌላ ሴት ፍለጋ፤ ሌላ ሴት ጋርም ሲሄዱ ተመሳሳይ ችግር በዚህንጊዜ ችግሩ የእኔ ነው ከማለት የሴቶች ነው ወደማለት ይደርሳሉ። ይህ በእንዲህ እያለ ደግሞ ዓለም ጥራዝ ነጠቅ፣ ኢሰብአዊ(ኢተፈጥሮአዊ) የሆነውን ወሲብ ለጊዜው ባያደርጉትም በእምሮአቸው እንዲያስቡት ብሎም እንዲለማመዱት በወሲባዊ ትዕይንቶች(ዛሬ ብዙዎችን በድብቅ ሱሰኛ ያደረገ) በመዳፈቸው ላይ በምትገኘው የስልክ ቀፎ ታቀርብላቸዋለች። ታዲያ የወንዱ ራስወዳድነት እና አልረዳ ባይነት ያንገሸገሻቸው ሴቶች እንዲሁም የሴቶቻቸው ፍላጎቶች እንቆቅልሽ የሆነባቸውም ወንዶች የኑሮ አጋር የወሲብ ጓደኛ ፍለጋ ወደራሳቸው ጾታ መምጣታቸው አይቀሬ ሆነ ሲሆንም እያየን ነው(ይህ የዓለም ወጥመድ ነው)። (እባካችሁ ችግሩን የለም ብሎ ከመካድ ተጨባጭ መረጃዎችን ይዘን ወደ ተፈጥሮአችን እንመለስ)ሰው አድርጎ ፈጥሮን እንደ እንሰሳ እንድንረዳዳም ከአንድ ሁለት አድርጎን በነጠላ(በራስወዳድነት) ወይም ለብዙ በልቅነት በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች ለዘር አስቦን በግብረሰዶማዊነት ፍጥረታችንን አምካኝ አንሁን። ይህም ካልገባን አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ባሰብሽ….የሚለው ይገባናል ….ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *