ገድለ አባወራ?

አባወራነት አንድ ያገባህ ዕለት የቤትህም ኃላፊ ስትኾን የሚሰጥህ ስም ቢኾንም እንኳ ስሙን የሚመጥን ማንነት ግን ለመያዝ ከጋብቻህ በፊትም ኾነ በኋላ እልህ አስጨራሽ ልምምድን ይሻል።

በትዳር (በአንዲት ሴት) መወሰንህ፣በውሃ ቀጠነ ለፍቺ አለመቸኮልህ ደግሞ በአባወራነት ማማ ላይ ለመድረስ ኹነኛ ነው፤ እንጂማ ትዳርን እንደ ጫማህ ክር ሲያሻህ የምታስረው አልያም የምትፈታው ከኾነ እንኳን ከማማው ልትደርስ ከሥሩም አትቀርብ።

አባቶቻችን ልጆቻቸውን በሥርዓት አሳድገው፣ ኃማኖታቸውን ጠብቀው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውንም አፍሰው ይኽቺን የመሰለች ድንቅ ሀገር ያስረከቡን ራሳቸውን ገዝተውና ቤታቸውን በቅጡ አስተዳድረው ነው።

አንተም ግብራቸውን መውረስ ካሻህ ዐለም ጊዜህን፣ ገንዘብህንና ምትክ የሌውን አእምሮህን ከምትበርዝበት ነገር ከእንቶ ፈንቶውም ራቅ ። አባወራ እንዳትኾን እንቅፋት የሚኾኑትንም ንቀስ ለምሳሌም፦

፩ኛ አንተ ራስህ
ቀድሞ በነበረህ ማንነት ዐዲሱን የአባወራ ኃላፊነት መወጣት አትችልምና ሥልጣንህን
፩፥ሀ አለማመን፣ አለመቀበል እና አለመለማመድ እንቅፋት ናቸው።
*አለማመን፦ አኹን ላይ በየመገናኛ ብዙኃኑ የምትሰማው፣ ተምረናል ብለው ማስትሬትና ዶክትሬት የጫኑት፣ ቀን ሰጥቷቸው ስልጣን የጨበጡት ኹሉ እየነገሩህ ያሳደጉህ አኹንም የሚነግሩህ ቤት በጋራ እንደሚመራ እንጂ አንተ የቤትህ መሪ መኾንህን አይደለም።

ስለዚህም እኔ አስረግጬ ለምነግርህ የአንተ የመሪነት ስልጣን ይኽ እንቅፋት ነው። “እኩልነት” እየተባለ ፉክክር በሚሰበክባት ዓለም፣ የወንዱና የሴቷ ሚና በተደበላለቀባት ዓለም፣ “እርሱ በምን ተሽሎ ነው የሚመራው” በሚባልባት ዓለም፣ ሰዎች ከተፈጥሮኣዊ እውነት ይልቅ ለጋራ ስምምነት ባደሉበት ዓለም የአባወራን መሪነት ማመን ይከብድሃል።
*መቀበል፦ ልብህ ያላመነውን ደግሞ አእምሮህ እንዴት ይቀበለዋል? እምሮህን ተጠቅመህ ሰውነትህን አዘህ ወደ አንድ ዓላማ ለመዘርጋት ያን ዓላማም ኾነ እርሱን ለማስፈጸም የተሰጠህን ጸጋ በእርሱም ያለን የራስነት ስልጣን መቀበል ያሻል።
*መለማመድ፦ አንድን ድርጊት በሰውነትህ ብልቶች ብትሠራውም(ብትለማመደውም) የፈለግከውን ውጤት የምታገኘው ግን በልብህ አምነህ በአእምሮህ ተቀብለህ ስትፈጽመው ብቻ ነው።

ስለዚህ ከምንም በላይ ራስህን በንባብ በተፈጥሮኣዊው እውቀት መገንባት ግድ ይልሃል። አንተ ባላመንክበት፣ ባልተቀበልከውና ባልተለማመድከው ሕይወት ስኬታማ አትኾንምና።

፩፥ለ አቅም
አምነህ የተቀበልከውን ልኑርህ ስትለው የአቅም ማነስ ይገጥምሃል። እነርሱም አእምሮኣዊ፣ መንፈሳዊና አካላዊ አቅም ናቸው።
* አእምሮኣዊ እቅም አልኩኝ ከቤተሰብ፣ ከማሕበረሰብ፣ ከንባብ፣ ከቤተክርስቲያን አልያም በመደበኛ ትምሕርት የምታገኘው ስለወንድ ኃላፊነት፣መሪነት፣ ራስነት ማወቅ የተገባህ እውነተኛና ተፈጥሮኣዊ እውቀት ነው። በእርሱም ውስጥ ስለተፈጠርክበት ዐላማና ሚና ማወቅና እውቀቱንም ማበልጸግ ሲቀጥልም ሚስትህን ማሳረፍ ትውልድንና ሀገርን መጥቀም የምትችልበት ነው። ይኽ ከሌለህ አባወራነትን ስታስበው ገና ይደክምሃል።

*መንፈሳዊ አቅም አልኩኝ በስነፍጥረትም ኾነ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመመርመር ክብርህን፣ ልዕልናህን ሳትረዳ ብትቀርና ራስህን ከእንሰሳ ብታስተካክል(እንሰሳት እንኳ መድረሻውን የሚያቅ አውራ ሲኖራቸው) አንተ ግን ከእነርሱ ብሰህ መረን ትኾናለህ። ስለዚህም ፈሪሃ እግዚኣብሔርን፣ ሰውን መውደድን በተለይም ደግሞ ሚስትህን እንደራስህ መውደድክን አትርሳ። ኾደ ሰፊነትን፣ታማኝነትን፣ ቃል ጠባቂነትን፣ ታታሪነትን፣ ለጋስነትን፣ ታማኝነትን ያዝ። ነገር ግን በዓላማህ፣በሚስትህ፣ በሀገርህ፣ በኃይማኖትህ ለመጣው ደግሞ የሚፋጅ እሳት መኾንክን በጀግንነትና በቆራጥነት የሚጋፈጥ ልብ ከሌለህ ተስፋ ትቆርጣለህ።

* አካላዊ አቅም አልኩኝ መንፈሳዊውንም ኾነ አእምሮኣዊውን ብቃት(አቅም) በግብር የሚገልጣቸው አካልህ ነውና ልትንከባከበው በንጽሕና(መሽሞንሞን ሳይኾን)፣ ልታጎለብተው (በስፖርት)፣ ከአላስፈላጊ ልማዶች(ሱስ) ልትጠብቀው ይገባሃል። አልያ ግን የአባወራነቱን ሥልጣን መሸከም የማይችል ልፍስፍስና ፍዝ ይኾናል።

አእምሮኣዊና መንፈሳዊ አቅምክን በንባብ፣ በጸሎትና በልምምድ ስታበለጽጋቸው አካላዊ አቅምህን ደግሞ በስፖርት ታዳብራለህ።
እነዚህን በአንድነት ቅርጽ አስይዘህ የሚፈልጉትን ስርዓት ተከትለህ መሄድ ግድ ይልሃል። ልብ አድርግ ድርጊቶችህ በስርዓት ካልታጠሩ ድካምህ ከንቱ ነው።

በራስህ በኩል ያለውን ለአባወራነት ተግዳሮት የኾኑትን እነዚህን አስወግደህ አምነህ በተቀበልከው የራስነት ጸጋ ስትመላለስ በአቅምህ(በልክህ) የተሰፋ በሚስትህም የሚወደድ ይኾንልሃል። አንተም የወንድ ልኩ የወንድ መለኪያው ቁና ትኾናለህ።
ብንኖር
፪ኛ ሚስትህ(የብዙ ምስኪኖች ፍርሃት)…. ይቆየን

Oct 13, 2018, 12:54 AM
አባወራ added 3 new photos.
ገድለ አባወራ? 1
ገድለ አባወራ? 2
ገድለ አባወራ? 3
አንተና የመሪነት ሚናህ

አንተ በቤትህ ውስጥ ሊኖርህ ስለሚችለው ሚናህ በቀደመው ጽሑፍ መለጠፌ ይታወሳል። ኾኖሞ ግን አንዳንድ ወዳጆቼ “በመምራቱና በማስተዳደር ሚናም ቢኾን ተፈላጊነቱ ያን ያክል የጎላ አይደለም፤ ዛሬ ዛሬ ሚስቱም ብትኾን ታግዘዋለችና ከዚህም የተነሳ አብዛኛውን ጊዜ ፈት(ቦዘን) ነው።” ስለማለታቸው ሀተታ፦

ወዳጄ ቤትህን ማስተዳደር የሙሉ ጊዜ ሥራ ነው። አንድ ቀን “እንዲህና እንዲያ ባለው ሥርዓት ሂዱ” ብቻ ብለህ የሚያበቃ አይደለም። በዚያ መንገድ እንዲጓዙ ማሰልጠን መጓዛቸውንም ማረጋገጥ፣ ከመንገድ ሲወጡም መመለስእንጂ።
የቤትህ አዛዥነት፣ መሪነት፣ አስተዳዳሪነት
ይኽ ያንተ ትልቁና ከባዱ ሥራ(ሚና) ነው። ዛሬ ዛሬ ወንዶች ሴታቆርቋዥ (Feminism) በኾነው እሳቤ፣አንድም በ”እኩልነት” ሰበብ አንድም በምስኪንነት አልያም በስንፍናና በንዝህላልነት ተወስደው ትተውታል። ታዲያ ትውልድ መረን ቢኾን ለምን ይገርመናል?

አባወራ ሚስቱንና ልጆቹን እግዚአብሄርን በመፍራት፣ በሀገር ፍቅር፣ በሰው አክብሮት፣….. በማሳደጉ ማንም የማይተካውን ሚና ይጫወታል። ስለኾነም አንተ የቤትህ አዛዥ፣ ናዛዥ፣ መሪ፣ አስተዳዳሪ ነህ። ለዚህ ደግሞ ምስክር ካሻህ የፈጣሪህን ትዕዛዝ ከቅዱሳት መጻሕፍት፣ የተፈጥሮን ምስክርነት ከራስህ ተፈጥሮኣዊ ባሕርይህ በማስተዋል መረዳት ትችላለህ።

ይኹን እንጂ ስልጣኔ ገብቶኛል፣ ጥበብም ተገልጦልኛል ብለህ ሚናህን ለክርክር(የኔነው አይደለም ስትል) ግዴታህንም ለድርድር(አንቺ ብትሠሪውስ ስትል) መዳረግ አምላካዊ ትዕዛዝን መናቅ፣ ግዴታህንም አለመወጣት፣ ትውልድንም መግደል፣ ማሕበራዊ አንድነትን ማፍረስ፣ ሀገርንም ማጥፋት ነው።

ወንድሜ! ማንኛውንም ተቋም እስኪ ተመልከት
ማሕበራዊ ኾኖ እድር ቢኾን መተዳደሪያ ደንብ ሲኖረው መሪውም ዳኛ ይባላል፤
ሰንበቴ ቢኾን እንዲሁ ደንብ ኖሮት መሪውም ሙሴ ይባላል፤ ድርጅታዊ ተቋምም ቢኾን መተዳደሪያ ደንብ ይኖረውና አስተዳዳሪው ደግሞ ሥራ አስኪያጅ፣ ዳይሬክተር ይባላል፤ ሀገር ቢኾን መተዳደሪያ ሕገመንግስት ይኖረውና መሪውም ጠቅላይ ሚንስትር/ፕሬዝዳንት ይባላል ..ወዘተርፈ።ኹሉም ተቋም የሚተዳደርበት ሥርዓትና አስተዳዳሪ በእርግጥ ስልጣን ያለው አሰተዳዳሪ (የይስሙላ አሉና) ይኖረዋል።
ትዳርምእንዲኹ ነው። ትዳር ተቋሙ ሲኾን አንተ ደግሞ የቤትህ ሕግ አውጪ፣ አስፈጻሚውና መሪው ነህ፤ ከዚህ ሚናህ የተነሳም መጠሪያህ አባወራ ነው።

አንተ በትዳርህ ውስጥ በተለይ በተሰጠህ ስልጣንና በስልጣንህም በምትጫወተው ሚና መጠን ትገለጻለህ። እርሱም በሥርህ ያሉትን የቤተሰብ አባላት ምነኛ ግብረገብና ብቁ ዜጋ አድርገህ በማፍራትህ ነው።

በአንተ አስተዳደር ሥር ያሉትን ሚስትህን ጨምሮ ሌሎቹንም የቤተሰብ አባላት እንደየጾታቸውና እድሜያቸው ልዩነት በሥርዓት ያድጉ ዘንድ ማሳደርህ ራሳቸውን አውቀው፣ ኾነውና አክለውም እንዲኖሩ ይረዳቸዋል። በተጨማሪም ሰውን የሚያፍሩ፣ ፈጣሪን የሚፈሩ፣ ለሀገር የሚሞቱ ለድሀ የሚራሩ ዜጎችን ታፈራለህ።

በሴታቆርቋዡ (Feminism) እሳቤ የተወሰደው የአኹኑ ዘመን ሕብረተሰብ ይኼንን ቤትህን ቅጠኛና ልከኛ አድርገህ የምታሳድግበትን ሥልጣን ከአምባገነንነት ጋር ያወዳጀዋል። ከዚህም የተነሳ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ቤታቸውን በቅጡ ለማስተዳደር የሚሞከሩ ወንዶች ሲበዛ “ተቆጣጣሪ” እና “በዳይ(abusive)” ይባላሉ።

ዐለም ላይ ያለውን የዛሬውን ጊዜ ትዳር ስትታዘብ ግን በትዳር ውስጥ ያለው የወንዶች የመሪነት ሚና መቀዛቀዝ(አለመኖር) የተቋሙን(የትዳርን) ሕልውና ሲፈታተነው ታያለህ። የሴቶች በትዳራቸው አለማረፍ(የሚያሳርፍ መሪ አለመኖር)፣ የፍቺ መጠን መጨመር፣ የልጆች ያለአባት ማደግ፣ መረን የኾነ ትውልድ መፈጠር… የዚኹ የወንዶች የቤት ውስጥ መሪነት መዳከም(አለመኖር) ነው።

ስለዚህም ይኼን ሚናህን በስንፍናም ኾነ በፍርሃት ላለመወጣት “ሚስትና ልጅ እግዚአብሄር ሲሰጥ ነው” ብለህ በሰበብ ገመድ ራስህን ተብትበህ ትውልድን አትግደል። ይልቅስ ተነስ ራስህን በሥርዓት አሠልጥን ከዚያም ሚስትህን ቀጥሎም ልጆችህን። ይኼን ስታደርግ ብቻ በሥነምግባር የታነጸ፣ በግብረገብም የተሞላ፣ ሰውን የሚያከብር፣ ፈጣሪውን የሚፈራ፣ ሀገሩንና ወገኑን ከመዝረፍ ይልቅ የሚሞትላቸውን ትውልድ ታፈራለህ። አልያ ግን ያልዘራኸውን መሰብሰብ፣ ያልሰበሰብከውንም ማከማቸት፤ ስታስበው ስንፍና ስታደርገው ደግሞ ሌብነት ነውና።

“ይኼን ማድረግ ፈተና የለውም ወይ?” እንዴታ ሚናህን ከባድ የሚያደርገው ምን ኾነና።
ፈተና ከየት/ከማን
፩ አንተ ራስህ የራስህ ፈታኝ
፪ ሚስትህ
፫ልጆችህ
፬ ቤተሰብ፣ ጓደኛ (ያንተም ኾነ የሚስትህ) ….. ብንኖር ይኼንንና የራሴን ተሞክሮ ….ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *