ጉርሻ ለሴቶች

ጉርሻ ለሴቶች 1

በጭራሽ የባልሽን ሚና ለመወጣት አትሞክሪ

ባልሽ እንደው በጠቅላላው ወንዳወንድ ወንድ ወይም የወንድነት ሚናውን አልወጣ ያለ ባል ቢሆንብሽ
በጭራሽ በጭራሽ እደግመዋለሁ በጭራሽ የእርሱን የባልነት/የወንድነት ሚና/ግዴታ ልወጣ ብለሽ እንዳታስቢ።

ጥያቄ፦እንዴ? ቤቱን ማስተዳደር ሲያቅተውስ ፣መወሰን ፣ልጆቻችንን በአግባቡ መቅጣት ቢያቅተው ቤታችን መፍረሱ ልጆቼስ ሥርዓት አልባ መሆናቸው አይደለምን?
ይህ ይሁንብሽ እያልኩኝ አይደለም። ቢሆንም ግን ከአንቺ የሴትነት፣ የእናትነት፣የሚስትነት ሚና በተጨማሪ በተፈጥሮሽ የሌለውን ሚና ልወጣ ማለትባንቺ ላይ የሥራ ጫና በተለይም ደግሞ የሚና መደበላለቅና በሕይወትሽም ግራ መጋባትን ይፈጥርብሻል። ከዚህ በላይ ደግሞ የእናትነት፣የሚስትነት፣የሴትነት ለዛሽን በማሳጣት የማይቀለበስ የጠባይ ለውጥ ያመጣብሻል። ሀዘን፣ትካዜ፣ብስጭት፣ተስፋመቁረጥ የዘወትር ጠያቂዎችሽ ይሆናሉ።
መቼም እህቴ እንኳን አንቺ አኔም ይህ እንዲሆንብሽ አልፈልግም።

እና ምን ላድርግ አለሽኝ?
ባልሽን፣ትዳርሽን፣ልጆችሽን ማትረፍ ትፈልጊያለሽ?
ባልሽ ወንዳወንድ ዘመዶች፣ጓደኞች ካሉት ለወንድነት ምሳሌ የሚሆኑትን በምክንያት(ቡና ጠጡ፣ጠበል ቅመሱ ሌላም) እያልሽ ባሌን ምከሩለኝ ሳይሆን ጨዋታው አንቺ ወደምትፈልጊው ቁም ነገር እንዲያመራ አድርገሽ ቁምነገሩን ለእነርሱ ትተሽ ሥራ እንዳለብሽ ይቅርታ ጠይቀሽ ዘወር። እነርሱ መሐከል ሆነሽ እንደወንጀል መርማሪ ላፋጥህ ብትዪ ድካምሽን ውሀ በላው። ይህ ካልሠራ ግን ከላይ ልትጠሪያቸው ካሰብሻቸው ሰዎች ለምትቀርቢው ባልሽም የሚቀርበውን መርጠሽ ችግርሽን በግልጽ ማካፈል።እንጂ በተቻለሽ መጠን ሚናሽን አትልቀቂ።…….ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *