አባወራ Blog

ስለትዳር የማታማክራቸው ሁለት ሰዎች 1 0

ስለትዳር የማታማክራቸው ሁለት ሰዎች

ሳተናው! ስለትዳርና ስለምትመርጣትም ሴት ጭምር አንስተህ ልታወያያቸው፣ ልታማክራቸውና ሀሳባቸውንም ልትቀበላቸው የማይገቡ በተለይ ሁለት ሰዎች አሉ። እነዚህም ምስኪንና ሴታውል ናቸው፤ “እንዴት?” እንዴት ማለት ጥሩ ምስኪን ስለሴት ያለው አመለካከት ከተፈጥሮ የራቀ፣ በፍርሃትና በአጉል”ፍቅር” የታጠረ፣ በ”ስልጣኔም” የታወረ...

ሁሉን አትብላ! 2 0

ሁሉን አትብላ!

ሳተናው! ምግብ የሚሠሩ ነጋዴዎች ደንበኞቻቸውን ነገ እና ከነገወዲያም ተመልሰው እንዲመጡ የሚያደርጋቸውን የምግብ ዓይነት ያዘጋጃሉ። ይኹን እንጂ ነጋዴዎች የገበያ ወረት ጠባቂዎች ናቸውና ካንተ ገንዘብ ከማትረፍ ያለፈ ብዙ ርቀው በመሄድ ምግባቸው በወደፊት ጤናህ ላይ ስለሚፈጥረው ጉዳት...

ሁሉ አይጠቅምምና፤ ያገኘኸውን ሁሉ አትብላ! 3 0

ሁሉ አይጠቅምምና፤ ያገኘኸውን ሁሉ አትብላ!

ሳተናው! አንተ በዓላማ ለዓላማ የምትኖር ሰው ነህና ከርዕይህ ሳትደርስ ሳታሳካውም እንዳትቀር አመጋገብህን አስተካክል። ምንም እንኳ ሁሉን መብላት ብትችልና ቢቀርብልህም ሁሉም ግን አይጠቅምህምና አትብላ። ይልቁንስ ከተመገብካቸው በኋላ ባንተ ላይ ስለሚያደርሱት ተጽዕኖ አስበህ መርጠህና ለይተህ ተመገብ...

እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ 4 0

እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ

ሳተናው! ይኼ የምሰጥህ ምክር ተረት ሰምቼ፣ ወድጄውም የምትርክልህ እንዳይመስልህ። የመጀመሪያ ደረጃ የዐይን ምስክር ኾኜ ያየሁት፣ በሁለተኛ ደረጃም የታዘብኩት አልፌ ተርፌም በሕይወት ካለፉበት ሰዎች ላይ ከሰበሰብኩት መረጃ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ደጋግሜ የ”አባቷ ልጅ” ስል ትሰማለህ...

"ትኅትና" የምርጫህ መለያ 5 0

“ትኅትና” የምርጫህ መለያ

ሳተናው! የሃያዎቹ እድሜዎች የወንድ ልጅ ከእውቀት፣ ከእድሜ እና ከልምድ ከዚህም የተነሳ ከሚገኘው ጥበብ አነስተኛ ክምችት እያለው ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒ ብዙ እንዳወቀ፣ እንዳስተዋለ እና እንደኖረም ሰው “ነኝ” የሚልበትና የሰውን ምክርም ከመስማት አሻፈረኝ የሚልበት እድሜ...

ሚስትህ ጥበቃ ትሻለችን? 6 0

ሚስትህ ጥበቃ ትሻለችን?

ሳተናው! ለወንድ ልጅ በመሠረተው ትዳር ሚስቱ ለኑሮ የሚያስፈልጋትን (አስቤዛ) ማቅረብ፣ ከማንኛውም አደጋ መጠበቅ እና ትውልድን ተክተው ያልፉ ዘንድ ዘርን መስጠት ተፈጥሮኣዊ ግዴታው ነው። ከእነዚህ ሦስቱ ኃላፊነቶቹ ታዲያ በተለይ የመጀመሪያው (ለቤቱ የሚያስፈልገውን አስቤዛ ማቅረብ) ሴቶች...

ራስህን ግዛ፤ ቃልህም ከግብርህ ይስማማ 7 0

ራስህን ግዛ፤ ቃልህም ከግብርህ ይስማማ

ሳተናው! ማደግ፣ መለወጥ መበልጸግም ትሻለህን? እንግዲያውስ ከቁሳዊ ስኬትህ በፊት ለፍላጎቶችህ ልጓም ለብልቶችህም ስርዓትን ሥራላቸው። አእምሮህ የሚያስበውን አይንህ ይመስክር፣ ምላስህም ይናገር፤ ምላስህ የተናገረውን እጅህ ይፈጽም፤ ሆድህ ላባውም ብቅልን አትፈልግ። አንተ የምታስበውና የምትናገረው መያዣ መጨበጫ ከሌለው...

"ነኝ"ን ተውና ኾነህ ተገኝ! 8 0

“ነኝ”ን ተውና ኾነህ ተገኝ!

ሳተናው! ዛሬ ዛሬ የምታየው ወንድ በአብዛኛው ስሜታዊ ነው። አብዛኞቻችን ያልኾንነውን እንዲህ “ነን”፣ “እንዲህ ነኝ” ብለን እናወራለን። እንዲህ የምንለው አንድም ከመኾን ማውራት ስለሚቀለን፣ አንድም ደግሞ በሰዎች ዘንድ (በተለይም በሴቶች ዘንድ) ተወዳጅነትን ለማትረፍ ነው። ? “አንባቢ...

ትዳር ይቅርብህ፦ አታግባም! ፫ 9 0

ትዳር ይቅርብህ፦ አታግባም! ፫

ሳተናው! በቀደሙት ሁለት ጦማሮች የጀመርኩትን “አታግባ” ምክሬን ዛሬ ልቋጨው። ትዳርህ ውስጥ ከሚገጥሙ ፈተናዎች የተነሳ ፍቺን እንደ አማራጭ አስበህ አትግባ ማለቴን ታስታውሳለህ። አዎን! አንተ ትዳርን ስታፈርስ ፈራሹ በተለይ ቤተሰብህ ቢኾንም ትውልድና ሀገርም ግን ተመሳሳይ ዕጣ...

ትዳር ይቅርብህ፦ አታግባ ፪ 10 0

ትዳር ይቅርብህ፦ አታግባ ፪

ሚስቴ ብትፈታኝስ ብለህ ተሰቅቀህ ፈጣሪ የሰጠህን ግዴታ(የወሲብ፣ የማስተዳደርና፣ የሚያስፈልገውን የማቅረብ) ግዴታህን ከመወጣት ቸል ብትል፣ ብትተወውም ትዳር ለፈሪዎች አይደለምና ይቆይህ፦ አታግባ! ሳተናው! ከዚህ ቀደም ፍቺ የማን መገለጫ እንደኾነ ተጫውተናል፦ አንተ የትዳርህ መሪው፣ የሚስትህ ራስ፣ የቤትህም...