ጸጋችንን በአግባቡ ለዓላማ

 

ሴትና ምላስ ወንድና ጉልበት
ቤት ያፈርሳሉ አላግባብ የኾኑ ‘ለት

ለሴት ልጅ ወሬ (ምላስ) ጸጋዋ ነው። በእርሱ ልጆቿ፣ ቤተሰቧ የሚፈልገውን ታውቅና ትንከባከብበትም ዘንድ ያስችላታልና።
ይኽ ስጦታዋ ታዲያ ከወንዱ አንደበትም ኾነ ከመስማት ችሎታው የተለየ ነው።

አስረጅ
፩ ሴቶች ምንም ሳይምታታባቸው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በአንድ ጊዜ ማውራታቸው
፪ አንዷ እያወራች የሌላዋ መግባት የሌላኛዋም መጨመርና ወሬውን “ማጣፈጥ”
፫ የአብዛኛው ወሬ ዓላማ መገናኘት፣ ናፍቆትን መወጣት፣ ፍቅርን ማጠንከር እንጂ ለተነሱት ጉዳዮች መፍትሔ መስጠት አለመኾን(አስፈላጊም አይደለም)
፬ አንድን መልዕክት ለማስተላለፍ ወይም ጉዳይ ለመግለጽ በተዘዋዋሪ መንገድ መጠቀም

፩ ሴቶች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በአንድ ጊዜ ማውራት

ይኼ ሴቷ እንደ መጋቢነቷ እንክብካቤ ፍለጋ የተለያዩ ጥያቄዎችን ይዘው ከሥሯ ለሚመጡ ልጆችም ኾነ የቤተሰብ አባላት ለማድመጥም ኾነ ምላሽ ለመስጠት ያስችላታል።

ይኹን እንጂ በአንድ ጊዜ አንድ ነገር ብቻ ለሚያስተናግደው የወንዱ አእምሮ ይኽ ከባድ ነው።

“ምንድን ነው የማይጨበጥ ነገር የምታወሪው” ማለቱም የማይቀር ነው።

፪ በአንዷ ወሬ ሌላዋ መግባት
ይኽ በርካታ የቤተሰብ አባላት በተለይም ሴቶች በኾኑበት ቤት የተለመደ ነው። አንዷበአንዷ ላይ ተደርባ ማውራትም የበለጠ መግባባትን ቢፈጥር እንጂ እንደ ስህተት አይታይም።

በወንዱ ዘንድ ግን ይኽ ትልቅ ንቀት ኢስነምግባራዊ(ዋልጌነት) ነው። ስለዚህም የባልሽን ንግግር አለማቋረጥ ማስጨረስም ተገቢ ነው።

፫ የወሬው ግብ

ለሴቶች ወሬ በስሞታ፣ በኃሜታ፣ በቅሬታ በሌላም መንገድ ቢቀርብ አብዛኛውን ጊዜ አገልግሎቱ አብሮነትን ከማጠንከር የዘለለ አይደለም።
በባልሽ ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም። ቅሬታዎችን መስማት መፍትሔንም መፈለግ ተፈጥሮው ነውና በቀላሉ ከአፍሽ ለሚዥጎደጎዱት ቃላት መፍትኼን ማሰብ መጨነቅም ይጀምራል። ስለዚህም ቅሬታዎችሽ መፍትሔ ለምትፈልጊላቸው ይኹን እንጂ “እንዲያው ዝም ብዬ ነው…”  እያልሽ ቃላትን አታውጪ።
፬ ቀጥተኛ ያልኾነ ወሬ
ወንዶች በደንብ ልንረዳቸው ከሚገቡ የሴት ምላስ ጠባዮች አንዱ እና ምናልባትም ዋነኛው ይኽ ነው። በተለይም ደግሞ በጾታዊ ቅርርብና ትውውቅ ዘንድ። ብዙዎች እየተፈላለጉ እንዳይቀራረቡ ና ወደ አንድነት እንዳይመጡ የሚያደርግ ወንዶች የማንረዳው የሴቶች ጠባይ ነው።
ይኼንን ጠባይ በተለይ ሴት አውሉና ዱርዬው በደንብ ያውቁታል። እኔም ከዚህ በፊት “ሴትን ያመነ ጉም የዘገነ” በሚል ርዕስ ጠቅሼዋለሁ።
ትሕትናሽ በአንደበትሽ ይገለጣልና ይኽን ፈጽሚ። የምላስሽ ጸጋጨባልሽን የማፍረስም ኾነ የመሥራት አቅም አለውና በአግባቡ ለዓላማው ተጠቀሚበት።
ወንድና ጉልበት
የወንድ ልጅ ጉልበትም እንደ ሴቷ ምላስ ኹሉ በዓላማ የተሰጠ ነው። እርሱም ወጥቶም ኾነ ወርዶ፣ አርሶም ኾነ ሸምቶ ለቤተሰቡ ምግብ፣ ልብስና መጠለያ እንዲያቀርብ፤ ሲቀጥልም ሚስቱን፣ ልጆቹን፣ ቤቱን፣ ሀገሩን ከጠላት እንዲታደግ፤ በስርዓትና በስነምግባር ይኖሩ ዘንድ የሚያወጣውን ሕግ እንዲያስፈጽምበት ነው።
፩ ወጥቶ ወርዶ ቤተሰቡ የሚያስፈልገውን ማቅረብ
ወዳጄ የተሰጠህን ጉልበት በስንፍና አታሟሽሸው፣ በሱስም አትጨርሰው። ወንድሜ ከራስህ አልፈህ ተርፈህ ለቤትህ፣ ለሀገርህ የሚተርፍ ጉልበት ሲኖርህ አለአግባብ ግን አታባክነው።
ይልቁንስ ዘወትር ራስህን ለመቻል፣ ቤተሰብህን(ቤትህን) ለመሥራት፣ ሀገርህንም ለመገንባት ትጋ እንጂ።
፪ ወዳጄ ጉልበትህ ጥቃትን መመከቻ፣ ጠላትህን ማንበርከኪያ እንጂ ሊከላከሉበት የሌላቸውን ደካሞች መደፍጠጫ፣ ወንድምህንም መግደያ አይደለም።
፫ አንተ አባወራ ስትኾን የቤትህ መሪ አስተዳዳሪም ነህ። በዚህም አንድ ሕግ አውጪ አካል ሕጉን የሚያስከብርበት አስከባሪ እንዳለው ኹሉ፤ አንተም ላወጣኸው የቤትህ ሕግ አስከባሪው አንተ ነህ።
ይኼን ታደርግም ዘንድ በግንባርህ ቁጣ፣ በትከሻህ ግርማ፣ በእጅህም ቅጣት ትፈራ ዘንድ ጉልበትህ አስፈላጊ ነው።
በአጉል ስልጣኔ ተመክተህ ጸጋህን ብትንቅ፣ ባትረዳው፣ ባትጠቀምበት፣ ብትቀያየርም ትርፉ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ እና ጸብ በመጨረሻም ፍቺ ነው። ጸጋሕን እወቅ፣ በአግባቡም ለተሰጠህ ዓላማ ተጠቀም….. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *