ፈሪሃ እግዚአብሄር ለአባወራ ምኑ ነው

እስከዛሬ በነበሩት ጽሑፎች ወስጥ አንድ ወንድ ወደ አባወራነት በሚያደርገው ጉዞ እና አባወራ ኾኖ በመቆየቱ ኺደት ላይ ስነሥርዓት(discipline) ትልቅ ሚና እንዳለው አይተናል። ምክንያቱ ደግሞ እርሱ ራሱ የስነሥርዓት አርአያ ካልኾነ ቤቱን፣ ሚስቱን፣ ልጆቹን በምንም ዐይነት በስነሥርዓት መርቶ ከዓላማ አያደርሳቸውምና ነው።

ይኽ ስነ ሥርዓት ከሚያስፈልግባቸው መስኮች አንዱ ታዲያ ከፈጣሪው ጋር ያለው ግንኙነት ነው።
አንተ ከፈጣሪህ ጋር ያለህ ግንኙነት ጤናማና አግባባዊ ሲኾን ብቻ ወደ እዚህች ምድር የመጣህበት ምክንያት የተፈጠርክበትም ዓላማ ይገባሃል።

እርሱ በወደደ ጊዜ፣ በፈቀደው ቦታ፣ ከመረጣቸው እናትና አባትህ አኹን ባለህበት የሰውነት መልክና ቅርጽ አስገኝቶኃል። በወደደ ሰዓትም፣ በፈቀደው ቦታ፣ በመረጠውም ምክንያት/ጥሪ ይወስድኃልና ፈጣሪህን ዘወትር ከጭንቀትና ከቅጽፈት(እቀሰፋለሁ ከማለት) የተነሳ ሳይኾን በፍጹም ፍቅር በፊቱ ልትቆም ይገባኃል።

ዘወትርም ቃሎቹ(ሕግጋቱ) የሚናፍቁህ፤ እንደሰማሃቸውና እንዳነበብካቸው መጠንም ወደ እርሱና ወደ ቅዱሳኑ ሕብረት ከፍታ የሚያሳድጉህ መኾን አለብህ።

መንፈሳዊ ነኝ ብለህ ቁጥር ማሟያ፣ ይኽ ነው ተብሎ የሚጠቀስ ሥራ የሌለህ በቀደሙት ሥራ ብቻ የምትመጻደቅ ፍሬ አልባ ገለባ የማታብብ የማታፈራም መኾን የለብህም።

ከፈጣሪ ዘንድ ስላለህ ዋጋ
አንድ ጀበና ወይም የሸክላ ድስት ከሸክላ አፈሩ ቡኮ ጀምሮ አልቀው እስከሚወጡ ለምንእንደሚጠፈጠፉ አያውቁትም ነበር። ተጠፍጥፈውሲያልቁ ግን የፈጁትን አፈር፣ ጊዜ፣ ውሃ፣ እሳት፣ ጥበብ የሚያውቅ፣ የተሠሩበትን ዐላማም የሚለይ፣ ዋጋቸውንም የሚወስን ሸክላ ሠሪውና ሸክላ ሠሪው ብቻ ነው።

ባንተም ሕይወት እንዲሁ ነው። ያንተን ትክክለኛዋጋ(self worth) ማወቅ ትፈልጋለህን? ወደ ፈጣሪህ ጠጋ በል። ዘወትርም ጆሮህን ከቃሉ ፊትህንም ከፊቱ አትመልስ። አንተ ከሠሪህ ዘንድ ያለህን ዋጋ የተፈጠርክበትን ዐላማም ሳታውቅ ልጆችህ ዋጋቸውን አይገነዘቡም።

ሴታቆርቋዡ እሳቤን (Feminism) የሚያራግቡ ሴቶች ስለሴቶች እኩልነት እንጮሃለን ይላሉ፤ ነገር ግን ምን ያክሎቹ ደካማ ወንድ ይፈቅዳሉ? አንዲትም ሴት ራሱን የማያስከብር፣ ከኃላፊነት የሚሸሽ፣ ተጠያቂነትንየሚጠላ፣ በpornogrphy የተለከፈ ወንድ አታደንቅም አትፈልግምም። ይኹን እንጂ አኹን እያሳደግን ያለነው እንደዚህ ዐይነት ወንድን ነው።

ሕብረተሰባችን እንደው በደመነፍስ(በትክክል የሚፈልገውን ነገር ስለማወቁ እጠራጠራለሁና) ፦በአንድ በኩል ሀገሩን ከጠላት፣ ከወራሪ፣ ከድህነት፤ ኃይማኖቱን ከከሃዲ፣ ከተጠራጣሪ፤ ትውልዱንም ከጥፋትና ከመረንነት የሚታደግለትን ጀግና የፈልጋል። ይኽ ጀግናም በስነምግባር የተመሰገነ ለሌሎች አርአያ የሚኾን ከሙስናና ከብልሹ አሠራር የጸዳ ደግ ግን ደግሞ ወሳኝና ቆራጥ እንዲኾንም ይምኛል።

በሌላ በኩል ግን በቤት ውስጥም ኾነ በትምሕርት ቤት የሚያሳድገው፣ የሚያስተምረውና የሚያበረታታው የእነዚህን ተቃራኒ ነው።

አንተ ቆራጥ ስትኾን ጨካኝ፣ ሥርዓት ሲኖርህ አካባጅ፣ ሥርዓትን ስትሻ(ከሰዎች) አምባገነን፣ ድፍረትን ስትለማመድ ስሑት(የተሳሳተ መንገድ የገባ)፣ ይሉሃል ግን ደግሞ ይኽ ማንነትህ እንደሚታደጋቸው ሲያውቁ ይፈልጉሃል።

አንተ በተፈጥሮ የተሰጠህን ጸጋ አውቀህና በልኩም አድገህ ዐላማህን ለማሳካት ከፈለግህ ከብዙኃኑ በተለየ መንገድ መጓዝ አለብህ። ይኼን መንገድ ደግሞ በTv, Radio በጋዜጣ፣ ከሕገ መንግስቱ፣ ከመጠጥቤት፣ ከጫት ተራ፣ ከትምሕርትቤት፣ ከUniversity ከsocialmedia … አታገኘውም። ይልቅስ በፈሪሃ እግዚአብሄር ተሞልተህ ከምታነበው የቃሉ ምንባብ በምትቆመው ቁመት እንጂ።

ልብ አድርግ! የምትኖረው በወንድ ላይ ባመጸ የአብዮትንም ማዕበል በቀሰቀሰ ሕብረተሰብ ውስጥ ነው። ብዙ ወንዶችም እንደ ትምሕርታቸውና እንደ ስልጣናቸው ሳይኾን በዚህ ማዕበል ተወስደዋል። ላንተም ሁለት ምርጫ አለህ
፩ኛ ከሕብረተሰቡ በሚደርስብህ ጫና የተነሳ ስልብና ፍዝ ኾነህ ዓላማህን ስተህ መኖር
፪ኛ ፈሪሃ እግዚአብሄርን ታጥቀህ በፍቅረ እግዚአብሄር ታጥረህ ለፈጠረህ ዐላማ ኖረህ ታሪክም ሠርተህ መሞት።

ምርጫህ ግን ሁለተኛው ከኾነ የምትታጠቀው ሙሉ ትጥቅ(logistics) ያለበት ውጊያ/ፈተና እንደሚጠብቅህ ስነግርህ በደስታ ነው።

በፈተና/በመከራ መንሠላልነት ወደ አባወራነት መጓዝን….. ይቆየን።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *