ርዕይህን የምትወስን ሳይኾን የምትደግፍ ሴት ምረጥ

ሳተናው!

ለዚህ ዘመን ወንዶች ትልቁ እንቅፋት ከርዕያችን ይልቅ ሴትን ማስቀደማችን ላይ ነው። ብዙዎቻችን የሊብራል ምዕራባውያን አስተሳሰብን በመገናኛ ብዙኃኖቻችን ተቀብለን በማስተጋባትና እርሱኑም በሕይወታችን በመኖር ተጠቂ ኾነናል።

ከምንኖርለት ርዕይ ከተፈጠርንለትም ዓላማ ይልቅ ብቻችንን ኖረን ኖረን በሕይወት መንገድ ላይ አንድ ቀን ላገኘናትን ሴት ተሸንፈን “ካላንቺ አልኖርም፣ ላንቺ ነው የምኖረው፣ ካንቺ ውጪ ሕይወት የለኝም” ብለን እናላዝናለን። ይኽንንም ዘመናዊ ዘፈኖቻችን፣ ፊልሞቻችን፣ ጥበባዊ ውጤቶቻችን በሙሉ ምስክር ናቸው።

ይኽም ምን ማለት ነው፦ በሕይወታችን ልንይዘው፣ ልናሳካውና ዋጋ ልንከፍልበት የተገባ ርዕይ ይኖረን ዘንድ ከመማርና ከመሠልጠን ይልቅ ሴትን አፍቅረን እንዴት በፍቅሯ እንደታመምን እና እንደተሸነፍን ጠዋትና ማታ በዘፈኑ፣ በፊልሙ፣ በግጥሙ…….. እንደጋግመዋለን፤ ደግሞም እንታመማለን።

ሳተናው!
የሚገርመው ነገር ታዲያ ለሴቷ እውነታው የዚህ ተቃራኒ መኾኑ ነው። ሴት ልጅ እርሷን ዓላማው፣ ግቡ፣ እና የሕይወቱ አጀንዳው ያደረገ ወንድ አይማርካትም(አፏ እንዲህ ብሎ ባይነገርህም)። “ደርሶብኝ ልየው” ካልክ ማየቱንስ እየው ልብህ እንዳይሰበር እንጂ።

አንተ ኑሮን ስታቅድ ሚስትህ ባንተ ክንድ ስር፣ ያንተን የሕይወት መቃን በመጠበቅ ለልጆችህ አርአያ መኾን አለባት። ይኹን እንጂ በእኩልነት አስተሳሰብ ተጠርንገህ ትዳሩ መቃን የለሽ ኾኖ አልያም በየጊዜው በሚቀመጠውና በሚነሳው የእርሷ መቃን ውስጥ ገብተህ ከኾነ ላንተ የሚኖራት ክብር እየቀነሰ መሄዱ እሙን ነው።

ስለዚህም በሴት ምርጫህ ርዕይህን የምትደግፍ፣ ትንሿን ጥረትህንና ስጦታህን የምታመሰግን መኾኗን እርግጠኛ ኹን። ያንተ ርዕይ የሰው መልክ፣ ይኹንታንና ጭብጨባን እያየ የሚገን እና የሚከስም ከኾነ የርዕይ ትርጉሙ ገና አልገባህም ማለት ነው።

“እኔ ግን ርዕይ የለኝም ነበር፤ እርሷ ብትውስንልኝስ?” የምትል ከኾነ ወዳጄ መጀመሪያ ከማግባትህ በፊት ርዕይ ይኑርህ። ከየት እንደተነሳና ወዴት እንደሚሄድ የማያውቅ ሰው እንዴት መድረሻው ወዳልታወቀ ጉዞው ሚስትና ልጆችን ይጨምራል? ዘወትር የዕለቱን አጀንዳ የሚሠራውንም ሥራ ዓለምና ፌስቡክ የሚሰጡት ሰው እንዴት ወደ ትዳር ይገባል?

በመጨረሻም ወንድሜ በዚህች አመንዝራ ዓለም ምክር ተነድተህ ሴትን ከማሳደድ ይልቅ ርዕይህን ሻ፣ ፈልግም ከዚያ እርሱን ለመጨበጥ ትጋ። እርሷ ለርዕይ እንዳለህ እና ለእርሱም የማይናወጥ አቋም እንዳለህ ወደብም እንደምትኾናት ስታውቅ ትመርጥሃለች።

አለበለዚያ ግን የሥራ መስክህን፣ የእርሷን ፊት እያየህ የምትቀያይር፣ የአንደበቷን እያመንክ የምትልፈሰፈስ ከኾነ ለራስህ መቆም የማትችል አንተ አይደለም ነገ ለሚመጡት ልጆቿ ለእርሷም የማትበጅ እንደኾንክ ትረዳለች።

የምትሄድበትን እይ፣ ወደዚያም ተጓዝ፣ የምትከተልህንም ምረጥ!

……ይቆየን

ለምስኪን ሕግ ሲወጣ፤ ለዱርዬው ግን የነበረውም ይፈርሳል

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *