2. በራስ መተማመንን በራስ ማበልጸግ

አባት ምትክ የለሹ ተፈጥሮአዊ የራስ መተማመን አሰልጣኝ ነው። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች በአካልም ባለመገኘትም ኾነ በተሳትፎ(በአካል ኖሮም ልጆቹን በማነጹ) በቤቱ ላይኖር ይችላል። በዚህን ጊዜ ከሚጓደሉት የልጆች የስብዕና እሴቶች ውስጥ አንዱ በራስ መተማመን ነው።

ይኽ ሲኾን ጉድለቱን መሙላት፣ራስህንም ማበልጸግ ያንተ እና ያንተ ሥራ ይኾናል። ማበልጸግ ያለብህን ሦስት መሠረታዊ ክፍሎችም መንፈስህ(ነፍስህ)፣ አእምሮህ እና አካልህ (ተክለሰውነትህ) ናቸው።

1. መንፈስህን አበልጸግ፦ አንተ ከሌሎች(ፈጣሪህ፣ሰዎች እና ሌሎች ፍጡራን)ጋር ተግባብተህ ተረዳድተህ የምትኖርበትን መንፈሳዊ እሴት መያዝ ለራስ መተማመንህ አይነተኛ ሚና ይጫወታል። መንፈሳዊነትህ ስለፈጠረህ፣ ስለራስክ፣ ስለሌሎችም ፍጡራን ትክክለኛ ማንነት እና አብሮ የመኖሪያውም መመሪያ ያሳውቅሃል። ምንም እንኳ ላንተ በተሰጠህ ሥራ ራስህን ችለህ የመሥራት ኃላፊነት ቢኖርብህም ከሌሎች ጋሮ ያለህን ሱታፌ ግን ጭርሱን ሊያስረሳህ አይገባህም። ይኽ ለሌሎች የምትዘረጋው እና ከሌሎች የምትቀበለው እጅ የአንተን በማሕበረሰቡ ውስጥ ያለህን ቦታ ከሰውም ፊት የመቆም አቅምም ይሰጥሃል።

ይኼ ማለት ግን የራስህ ጊዜ አይኖርህም ማለት አይደለም። የራስህ የኾነ የጥሞና፣የጸሎትም ኾነ የተመስጦ ጊዜ ቢኖርህ አቋምህን ውሎህን ልትፈትሽበት ትችላለህ። ከሰዎች ምስጋናን፣ መደነቅን፣ ሳትፈልግ በራስህ መቆም አለብህና።

2. አካልህን ሰውነትህን ጠብቅ፦ ከፈጣሪህ የተቸረህ ምንም ዓይነት አቋም ያለው ተክለ ሰውነት ቢኖርህ አመስግነህ ልትቀበለው፣ልትንከባከበውም፣ብሎም ወደ ሚፈለገው ብቃት ልታሳድገው ይገባሃል። ያልተቀበልከውን ተፈጥሮህን መንከባከብ አትችልም።ባልተንከባከብከው ሰውነትህም የራስ መተማመን ሊኖርህ አትችልምና።

የተስተካከለ እና ንጽሕናውን የጠበቀ የሰውነት አቋም ይኑርህ። “ምን እኔ እኮ አጭር ነኝ፣ ረጅም ነኝ፣ ጥቁር ነኝ …. ..” ሳትል የሰጠህን አመስግነህ ማጎልበት ማለት ነው። ስትፈጠር ከሴቷ አንጻር ስትታይ ከደረትህ ሰፋ ከወገብህ(ከዳሌህ) ጠበብ ከጡንቻዎችህም ፈርጠም ያደረገህ ያለምክንያት አይደለምና ይኽንኑ ጠብቀው አበልጽገውም(አዳብረውም)።

እርግጥ ነው በቀደመው ጊዜ ኑሮ እራሱ ለወንድ ልጅ ትልቅ የእንቅስቃሴ፣ የጥንካሬ እና የአካል ብቃት ማትረፊያ ነበር። አኹን ግን ይህ ባለመኾኑ ጊዜን እና ቦታን አስማምተህ ለሰውነትህ የሚበጅ ማጎልመሻ መሥራት ይገባሃል። አልያ ግን እንኳንስ ለችግር ቀን የሚውል ጉልበት ይቅርና ከተራክቧችሁ የሚገኘውን የደስታ ማዕበል መቋቋምም ይሳንሃል(ወደፊት የምናየው)።

3. አእምሮህን በጥበብ እና በእውቀት ማሳደግ፦ በጥበብ እና በእውቀት ስታድግ በራስ መተማመንህን ይጨምራል። አእምሮህን ለማሳደግ መማር የተገባህ ቢኾንም የመማርህ መታወቂያ ግን ዓለም የምታድለው የምስክር ወረቀት ሳይኾን የአንተ ትጋት እና በትጋትህም የቀሰምከው እውቀት ነው።

ቢላዋ ብረት ነው ስለቱ ሲደንዝ ከሌላ ቢላዋ ጋር ስታፋጨው ላዩ እየተሞረደ ስለቱ ይወጣል። ላንተም እንዲሁ ነው፤ አብረህ የምትውላቸው ሰዎች ዕድሜ ያስተማራቸው መከራም የመከራቸው ሲኾኑ በእውቀት እና በጥበብ ይቀርጹሃል፣ ይስሉሃል። ቢላዋ ቢላዋን እንደሳለ አባወራንም አባወራ ይቀርጸዋል።

እንደምታስተውለው ለራስ መተማመንህ እድገት በመንፈሳዊነትህ ከየት እንደመጣህ፣ ለምን እንደመጣህ፣ ወዴትስ እንደምትሄድ፣ ከአካባቢህ ጋርም የተፈጥሮን ሕግ ተከትለህ እንዴት እንደምትኖር ትረዳለህ። በአእምሮህም ጥብበ የተሰጠሁን ስጦታዎች ኹሉ በብልሃት ለላቀ ኑሮ ትጠቀምባቸዋለህ። የአካል ብቃትህ ሲደረጅ የተስተካከለ ቁመና ሲኖርህ ደግሞ ምድራዊ ውጣውረዶችህንም ኾነ ደስታህን መወጣት እና ማስተናገድ ይቻልሃል።

ጥንቃቄ!!
መንፈሳዊነትህን፣ የአእምሮህን እና የአካል ብቃትህን በአንድነት አሳድግ። አልያ ግን የአካል ብቃትህ አይሎ መንፈሳዊነትህ እና እውቀትህ ተዳክመው ዱርዬ እንዳትኾን።ከሴት የሚያኖር እውቀት አለኝ ብለህ መንፈሳዊነቱን አጓድለህ ስልጣኔም መስሎህ ለሴት-አውልነት እንዳትዳረግ። ዐለማዊው እውቀትን ንቀህ፣ አካልህንም ከመንከባከብም ኾነ ከማጎልመስ ርቀህ አጉል መንፈሳዊነትን ይዘህ የወጣለት ምስኪን እንዳትኾን ተጠንቀቅ።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *