ለባልሽ ሚስት እንጂ ….

በምንም ዓይነት መልኩ ባልሽ እህቴን ትመስዪኛለሽ የእናቴም ምትክ ነሽ ቢልሽ አቀረበኝ፣ ወደደኝ ብለሽ እንደ እኩያ እህቱ በቤት ውስጥም ሆነ ውጪ ባሉት ላይ ይገባኛል እና ያገባኛል ካንተም አላንስም እያልሽ መፎካከር መጨቃቅ አንዳንዴም ግብግብ መግጠም አግባብ አይደለም። እንደ እናቱም ውጪ ቢያመሽ በሃዘኔታ ይመቱሃል፣ ይሰርቁሃል፣ይገጩሃል ወይም በተቆጣጣሪነት መንፈስ ለምን አመሸህ የትስ፣ከማንስ ጋር እያልሽ አንቺም ተሳቀሽ እርሱን አታሳቂው አልያም ክፉ እና ደግ እንደማይለይ ህፃን የረገጥከውን የቀመስከውን ካልነገርከኝ አትበይው።

ከእዚህ ይልቅ እንደ እህቱም ሳትጨቃጨቂ ከእርሱ የምትፈልጊውን ነገር ብቻ አሳውቂው። እንደ እናቱም ሳታሳቅቂው የሚያስፈልገውን አድርጊለት። ከምንም በላይ ግን ሚስቱ ነሽና ከአፉ የሚወጣውን ቃል ጠብቂለት። የምንዴት(ም…..ን? እንዴት?) ንግግሮችን ካንቺ አርቂ። ያገባሽው አዋቂ፣ሙሉ ሰው ነውና የሚሄድበትን የሚደርስበትን የሚጎዳኘውን(ጓደኛ የሚያደርገውን) ካላወቅሁ ካልወሰንኩ አትበይ። አልያ ግን ለእያንዳንዱ ከእልፍኝ እስከ መኝታ ቤት ለሚሰራቸው ሥራዎች ያንቺን ማስተማመኛ(approval) የሚጠብቅ ይሆንና በራስ መተማመኑ ይቀንሳል፤ላንቺም ህይወት ያወቅሽው እና የወሰንሽው ይሆናልና ጣዕሟ አልጫ ይሆንብሻል፤ምክንያቱንም ሳታውቂው እየወደድሽው የፍቅርን ጥፍጥና(intimacy) ታጪበታለሽ።

*****አስተውይ ሁልጊዜም ሚስቱ ሁኚ።*****
*****በሚስትነትሽም ቃሉን አክብሪ።*****
ልብ በይ ወንድ ፈጣሪ በውበት አሳምሮ እና አድምቆ የፈጠረለትን ሴት ሲያይ መደነቁ ግልጽ ነው። ያችን ሴት አግብቷት ሲኖር ግን ልቡን የምትገዛውና ወንድነቱን የምታጎላው ስትታዘዘው ነው።
ስትታዘዢው ፦ 1 ወንዳወንድነቱ
2 በራስ መተማመኑም ይጨምራል
3 በተሰማራበትም መስክም ስኬታማ ይሆናል
“የሰውን ዉሎ አዳሩ ያደባባይ ስኬቱን ትዳሩ ይወስነዋል” ይባላል።

*****በተለይ በተለይ ደግሞ*****
አንቺን መውደድና ማስደሰት ከፈጣሪው የተሰጠ ግዴታው ብቻ ሳይሆን እርሱን ራሱ ደስ የሚያሰኘው እና የሚኖርለት የኑሮው ምክንያት ይሆንለታል።
እንግዲህ እወቂበት…..ይቆየን።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *